
ne Healthy Society International
Veterinarians caring for animals and people


ተልእኮአችን
በውሻ ንክሻ ተላላፊ የሆነውን የእብድ ውሻ በሽታን በመቆጣጠር
የሰው ህይወትን ማዳን
አንድ ጤናማ ሀብረተሰብ ድርጅት (One Healthy Society) የሚሰራው ለሰዎችና ለእንስሳት የተሻለና፣ ደህንነታቸው ተጠብቆ በአንድ ላይ የሚኖሩበትን ዓለም ለመፍጠር ነው። ዋና አላማችን በኢትዮጵያ በውሻ ንክሻ የሚተላለፈውን የእብድ ውሻ በሽታን የክትባት ዘመቻን በማድረግ እና በቀዶ ጥገና ማመክን የባለቤት አልባ ውሾችን ቁጥር የመቀነስ ስራ አገልግሎት በመስጠት ነው።
ድርጅታችን ልምድ ባላቸው የእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎች የሚመራ ሲሆን ፣ እነሱም ለዚህ መርህ አዎንታዊ ለውጥ ለማመጣት በጥልቅ ቁርጠኝነት የተሞሉ ናቸው።
ግባችን ተግባራዊና በተሞክሮ የተፈቱኑ መፍትሄዎችን በመጠቀም፣ በየዓመቱ በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን እንዲቀንስ አልፎም እዲጠፋ ማድረግ እና የባለቤት አልባ እንሰሶችን ቁጥር መቀነስ ነው።

የእብድ ውሻ በሽታ ምንድን ነው?
የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) በቫይረስ የሚነሳ በሽታ ሲሆን፣ በክትባት 100% መከላከል የሚቻል በሽታ ነው። ነገር ግን፣ በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ 59,000 ያክል የሰው ህይወት ያጠፋል። በሽታው ባለባቸው ውሾች ከተነከሱት ውስጥ 40% የሚሆኑት ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ናቸው። የእብድ ውሻ በሽታ በዓለም ላይ በጣም አስፈሪ እና አደገኛ በሽታ ሲሆን፣ የበሽታው ምልክቶቹ ከታዩ በኋላ 100% ሞት ያስከትላል ።
በ One Healthy Society International (OHSI) የእብድ ውሻ በሽታን ለመቆጣጠር እና ከዚህ አስፈሪ በሽታ የሚመነጩ አላስፈላጊ ህመሞችንና ሞትን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንሰራለን።
የእብድ ውሻ በሽታን ለመቆጣጠር፣ ቢያንስ 70% ውሾች መከተብ አስፈላጊ ነው። በ One Healthy Society International ውስጥ የውሻ ክትባት አስፈላጊነትን ለማበረታታትና እንዲሁም በተቻለ መጠን ብዙ ውሾች እንዲከተቡ ለማረጋገጥ በትኩረት እንሰራለን።
ከአካባቢ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር የክትባት ዘመቻዎችን እንደምናደርግና የውሻ ባለቤቶችን እንስሳቸውን ማስክተብ እንደሚያስፈልጋቸው የማበረታታት ስራን እንሰራለን። ከክትባት በተጨማሪ፣ ድርጅታችን በቀዶ ጥገና የሚፈፀም ማምክን በማድረግ ተግባራዊና ሰብአዊ የእንስሳት ብዛት መቆጣጠር ላይም ያተኮራል።
ውሾችን በመከተብና በማመከን የውሻ በሽታ መተላለፍን መከላከልና የውሾችንና የሰዎችን ህይወት ለማሻሻል እንችላለን።

የእብድ ውሻ በሽታ በኢትዮጵያ
በየዓመቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በግምት 2,700 ያክል የሰው ህይወት በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ይጠፋል።
የእብድ ውሻ በሽታ መተላለፍን ለመከላከል ውሾች በተስፋፋ ሁኔታ መከተብ አለባችው ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የውሾች ክትባት ደረጃ ከሚጠበቀው በላይ ዝቅተኛ ነው ።
በአንድ ጤናማ ህብረተሰብ ውስጥ፣ የእብድ ውሻ በሽታ (rabies) በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ከባድ አደጋ በግልጽ እናውቃለን። ስለሆነም ለእብድ ውሻ በሽታ ክትባት መዳረሻን ለማሻሻል እና ህዝቡ የዚህን አደገኛ በሽታ መከላከል አስፈላጊነት እንዲያውቅ ለማበረታታት በቁርጠኝነት እንሰራለን።
ጥረታችን በኢትዮጵያ በውሻ ንክሻ ምክያት የሚተላለፈውን የእብድ ውሻ በሽታን ለማስወገድ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚያደርግ ታላቅ ተስፋ አለን።



መርሃችን
የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመጠቀም የእብድ ውሻ በሽታ ችግርን ለመቅረፍ ቆርጠን እንሰራለን። ከማህበረሰብ ተደራሽነት እስከ የክትባት ዘመቻዎች፣ ከእብድ ውሻ ነጻ የሆነ አለም ለመፍጠር እንጥራለን።
የውሾች ክትባት ዘመቻ
ህብረተሰቡን ማስተማር
ባለቤት አልባ ውሽችን መቀነስ
ድርጅታችን ሰዎችንና እንስሳትን ከእብድ ውሻ በሽታ አደጋ ለመጠበቅ ሰፊ የውሾች ክትባት ዘመቻዎችን እንሰራለን።
ህብረተሰቡን እንዴት የእብድ ውሽ በሽታን መከላከል እንደሚቻልና እንዲሁም ሰለ ኃላፊነታዊ የእንስሳት ባለቤትነትን ማስተማርና ማበረታታት የሥራችን ዋና ክፍሎች ናቸው።
ከፍተኛ መጠን ባለው የቀዶ ጥገና ማምከን አማካኝነት የባለቤት አልባ ውሾችን ችግር ለመቅረፍ ቆርጠን ተነስተናል። የመጨረሻ አላማችን ለሰውም ሆነ ለእንስሳት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ አካባቢ መፍጠር ነው።

Who we are
Dr. Alem Terefe is a highly experienced veterinarian with a wealth of expertise in animal welfare. She has devoted a significant portion of her career to serving at the New York City animal shelter and the American Society for Prevention of Cruelty to Animals, where she honed her skills in high-quality, high-volume spay/neuter procedures, herd health management, and pet overpopulation control. Dr. Terefe's unwavering commitment to animal welfare inspired her to establish OHSI Inc, an organization dedicated to eradicating human rabies in Ethiopia and beyond.


ቀዳሚ ስራዎቻችን







